ድምፅ አልባው ሞገድ መጽሐፍ


ድምፅ አልባው ሞገድ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ኅብረት (ኢቫሱ) በሀምሳ አመታት ውስጥ የተጓዘበትን ታሪካዊ ጉዞ፣ በወንጌል አገልግሎትና በተማሪዎች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ዘላቂ በረከት፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያን የነበረውን አበርክቶት በስፋት የሚዳስስ ድንቅ ሥራ ነው። በኢቫሱ የጅምር ዘመን በነበሩና በዕድገቱም ውስጥ በቆዩ አገልጋዮች በተገኘ ተአማኒ መረጃ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ ለትውልድ የሚተላለፍ ትልቅ የታሪክ ሰነድ ነው። ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አጥኚዎች፣ ለቀድሞና ለአሁኑ የኢቫሱ አባላት፣ እንዲሁም የወንጌል አገልግሎት እንቅስቃሴ ታሪክን ማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም አንባቢ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመከር መጽሐፍ ነው።

የድምፅ አልባው ሞገድ መጽሐፍ መደበኛ ዋጋው $30 ሲሆን፣ መጽሐፉን በመግዛት ለኢቫሱ (EvaSUE) አገልግሎት ተጨማሪ ድጋፍ ወይም ስጦታ ለማበርከት ከፈለጉ፣ ከታች ያለውን የተጨማሪ ድጋፍ ማድረጊያ ሊንክ ይጠቀሙ። የምታደርጉት በጎነት የኢቫሱን የተማሪዎች አገልግሎት በኢትዮጵያ ለመደገፍ በቀጥታ ይውላል። በተጨማሪም ከአንድ በላይ መጽሐፍ በመግዛት ለሌሎች በስጦታ መልክ በመስጠት የመጽሐፉን ተደራሽነት ማስፋት እና ኢቫሱን መደገፍ ይችላሉ።